አርእስት የሚለው ቃል ችእስ የሚለው ቃል ብዙ ቁጥር ሲሆን ትችጉሙም አለቆች ማለት ነው። የግሥ አለቆች ወይም መሪዎች የተባሉትም ከ’ሀ’ እስከ ‘ፐ’ ድረስ ያለውን የግእዝ ግሥ ሁሉ የራሱን የአረባብ ስልት ጠብቆ የእነርሱን የአረባብ ባህርይ ተከትሎ ስለሚሄድ ነው። አርእስት ግሥ ቁጥራቸው ስምንት ሲሆን እነዚህም የሚከተሉት ናቸው።
ሀ, ቀተለ--- ገደለ ሠ, ባረከ--- አመሰገነ
ለ, ገብረ--- ሠራ ረ, ዴገነ--- ተከተለ
ሐ, ቀደሰ--- አመሰገነ ሰ, ክህለ--- ቻለ
መ, ተንበለ--- ለመነ ቀ, ጦመረ--- ጻፈ
የአርእስት መለያወች
እነዚህ ከላይ የተገለጹት የግሥ አለቆች አንዳአው ከአንዳቸው የሚለዩበት የራሳቸው የሆነ ባህርይ አላቸው። እነዚህንም መለያወች ከዚህ በታች እመንደሚከተለው ከፍለን እናያቸዋለን።
1, የሆሄ ብዛት
2, የሆሄ ቅርጽ
3, ሥርዓተ ንባብ / መጥበቅ መላላት/
በዚህም መሠረት የግሥ አለቆች ባህሪያቸውን እንደሚከተለው እናያለን።
ሀ, ቀተለ፡-
ሦስት ሆሄያት ብቻ አሉት
ሦስቱም ሆሄያት ግእዝ ብቻ የሆኑ በግእዝ የተነሳ
ላልቶ ይነበባል
ለ, ቀደሰ፡-
ሦስትና ከዚያ በላይ ሆሄያት ያሉት
በግእዝ የተነሳ / መካከሉ ግእዝም ሳድስም ይሆናል/
ጠብቆ የሚነበብ
ሐ, ገብረ፡-
ሦስት ሆሄያት ብቻ ያሉት
መካከሉ ሳድስ የሆነ በግእዝ የሚነሳ
ላልቶ የሚነበብ
መ, ተንበለ;-
አራትና ከአራት በላይ ሆህያት ያሉት
መነሻው ግእዝ መካከሉ ሳድስና ግእዝ የሆነ
ላልቶ የሚነበብ
ሠ, ባረከ፡-
ሦስትና ከዚያ በላይ ሆህያት ያሉት
በራብዕ የተነሳ / መካከሉ ግእዝ ሊሆንም ላይሆንም ይችላል/
ላልቶ የሚነበብ
ረ, ዴገነ፡-
ሦስትና ከዚያ በላይ ሆሄያት ያሉት
በኃምስ የተነሳ / መካከሉ ግእዝ ሊሆንም ላይሆንም ይችላል/
ላልቶ የሚነበብ
ሰ, ክህለ፡-
ሦስት ሆሄያት ብቻ ያሉት
መነሻው ሳድስ የሆነ / ድኅረ መነሻው ሁልጊዜም ሰድስ ነው/
ላልቶ የሚነበብ
ቀ, ጦመረ፡-
ሦስትና ከዚያ በላይ ሆሄያት ያሉት
በሳብዕ የተነሳ
ላልቶ የሚነበብ
No comments:
Post a Comment