በዚህ የትምህርት ደረጃ ለአጠናነፀ ይረዳን ዘንድ ግሶችን በአራት ክፍላት ከፍለን እንመለከታቸዋለን። ነገር ግን ሌሎች መጻህፍ ከዚህ በተለየ መልኩ ከፍለው ሊመለከቷቸው ይችላል።
፩, ገቢር ግሥ፡- ይህ የግሥ ዐይነት ቃላትንና ሐረጋትን መሳብ የሚችል የአድራጊ ድርጊት የሚገለጽበት የግሥ ዓይነት ነው። በዐረፍተ ነገር ውስጥ ሁልጊዜ ገቢር ስሞችን ይወስዳል።
ምሳሌ፡- ገብረ ሠራ ሰጠቀ ሰነጠቀ
ዘገበ ሰበሰበ ፈኀረ አጨ
ጼሐ ተረገ መሀረ አስተማረ
መርሐ መራ ለበወ አስተዋለ
ፆረ ተሸከመ አርኀወ ከፈተ
ዖደ ዞረ ወዘተ…
ቃላትንና ሐረጋትን ሲስቡም በምሳሌ እንደሚከተለው እናያቸዋለን።
አብርሃም ገብረ ግብረ ሠናየ
በቀዳሚ ገብረ እግዚአብሔር ሰማየ ወምድረ
ቀርነ ነፍሐ
ወከለልዎ ክሳዶ ወዘተ…
፪, ተገብሮ ግሥ፡- ይህ የግሥ ዐይነት በገቢር ግሥ ላይ ባዕድ ፊደል “ተ”ን በመነሻ በመጨመር የሚመሠረት ሲሆን የተደራጊ ድርጊትን ይገልጻል። ይህ የድሥ ዓይነት ገቢር ግሥን አትስብም።
ምሳሌ፡- ገብር ተገብሮ ገቢር ተገብሮ
ገብረ ተገብረ ቀተለ ተቀትለ
ዘገበ ተዘግበ ጸሐፈ ተጽሕፈ
ሰብሑ ተሰብሑ መሐሩ ተመሐሩ
ሤመ ተሤመ ወዘተ…
ማስታወሻ፡- ሀ, በ”ተ” የሚጀምር ግሥ ሁሉ ተገብሮ ግሥ አይደለም።ምሳሌ፡- ተንበለ/ለመነ፣ ተሞገሰ/ባለሟል ሆነ፣ ተምዐ/ተቆጣ፣ተመነየ/ተመኘ፣ ወዘተ
ለ, በ”ተ” የሚጀምር ግሥ ተገብሮ የሚሆነው ተን አስወግደን የቀረው ገቢር ግሥ የሚሆን ከሆነ ብቻ ነው።
፫, ነባር አንቀጽ፡- እነዚህ የግሥ ዓይነቶች ከገቢርም ሆነ ከተገብሮ ግሦች ለየት ያሉ ናቸው። ቁጥራቸውም እንደ ገቢርና ተገብሮ ግሦች ብዙ አይደሉም።
ምሳሌ፡- ሀ, ውእቱ--- ነው፣ ነበረ፣አለ፣ ኖረ
ለ, ቦ--- አለ፣ ኖረ፣ ነበረ
ሐ, አኮ--- አይደለም፣
መ, አልቦ--- የለም፣ አልኖረም፣ አልነበረም
እነዚህ ከገቢርና ከተገብሮ ግሦች የሚለዩበትና የሚመሳሰሉበት ሁኔታ አለ።
የሚለያዩበት፡- 1, መድረሻ ፊደሉ ካእብና ሳብዕ መሆኑ
2, በካልዓይ፣ በዘንድና በትዕዛዝ አንቀጽ አለመገኘታቸው
3, ከንዑስ አንቀጽ እስከ ቦዝ አንቀጽ ድረስ ያሉትን እርባታዎች አለማካተቱ
የሚያመሳስላቸው፡- 1, ማሰሪያ አንቀጽ መሆን መቻላቸው
2, በአሥሩ መራሕያን መዘርዘራቸው
፬, ግዑዝ ግሥ፡- ይህ የግሥ ዓይነት ደግሞ በቅርጸ ቀለማቱ ገቢር ግሥን ሲመስል ገቢር ቃላትን ባለመሳቡ ተገብሮ ግሦችን ይመስላል። ስለሆነም ይህንን የግሥ አይነት ተን በመጨመር ወደ ተገብሮ ግሥ መቀየር አይቻልም። ይህም የሆነው በራሱ የተገብሮ ግሥ ፀባይ ስላለው ነው። ብዙ መጻሕፍት ግዑዝ ግሥን በተገብሮ ግሦች ውስጥ ያካትቱታል።
ምሳሌ፡- ኖመ--- አንቀላፋ፣ተኛ ሞተ--- ሞተ
ቆመ--- ቆመ ፆመ--- ፆመ
ሖረ--- ሄደ ደግደገ--- ከሳ
ሰከበ--- ተኛ ጎየ--- ሸሸ ወዘተ…
መራኁት(የግሥ መነሻዎች)
መራኁት የሚለው ቃል መርኆ የሚለው ቃል ብዙ ቁጥር ነው። ይኸውም “አርኀወ = ከፈተ“ ካለው የግእዝ ግሥ የተገኘ ነው። ስለዚህ መርኆ ማለት መክፈቻ ማለት ሲሆን መራኁት መክፈቻዎች ማለት ነው። መራኁት የተባሉትም የግሥ መነሻ ፊደላት ናቸው። በግእዝ ሰዋስው ግሦች የሚነሱት በአምስት ፊደላት ብቻ ነው። አነዚህም መራኁት ይባላሉ። አነርሱም ግእዝ፣ ራብዕ፣ ኃምስ፣ ሳድስና ሳብዕ ናቸው። የግእዝ ግሥ ሁሉ በእነዚህ ይጀምራል እንጅ በካዕብና በሣልስ አይጀምርም።
ምሳሌ፡- በግእዝ__ ቀተለ፣ ሰከበ፣ ሰጠቀ፣ አፍቀረ፣ አርኀወ፣ መርሐ፣ አኀዘ፣ ጎንደየ፣ ኈለቈ
በራብዕ__ ባረከ፣ ሳቀየ፣ ማህረከ፣ ጻህየየ፣ ፃዕደወ፣
በኃምስ__ ሴመ፣ ሤጠ፣ ኄሰ፣ ኤለ፣ ጼሐ፣ሴሰየ፣ ዴገነ፣ ጌገየ፣ ሌለየ፣ ቄቅሐ
በሳድስ__ ብህለ፣ ርእየ፣ ጥዕየ፣ ውኅዘ
በሳብዕ__ ጦመረ፣ ኖመ፣ ሖረ፣ ሎለወ፣ ቆመ፣ ኖለወ፣ ጾመ፣ ኆሠሠ
ማስታወሻ፡ 1, ግሦች ሁሉ መነሻቸው ይለያይ እንጅ መድረሻቸው ሁልጊዜ ግእዝ ቀለም ነው። እንበለ ይቤ
2, የግሥ ሆህያት ብዛት ቢበዛ ከሰባት አይበልጥም ቢያንስ ከሁለት አይወርድም።
ምሳሌ፡- ዔለ፣ ሤጠ፣ ሁለት ሆህያት
አስተስነአለ= አስተስነአለ ባለሰባት ሆህያት
በግእዝ ቋንቋ ትምህርት የግሦችን ዝርዝር ለመማር ስንጀምር ግሦች በዝርዝር ወቅት የሚያሳዩትን ፀባይ መሠረት በማድረግ ከዚህ እንደሚከተለው እንከፍላቸዋለን።
ሀ, አርእስት ግሥ
ለ, ሠራዊት ግሥ
ሐ, ስረይ ግሥ
No comments:
Post a Comment